ራዕይ
መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብና የአገር ውስጥ ገበያን በማረጋጋት በ2022 ዓ/ም በተገልጋዩ ኅብረተሰብ ተመራጭ ሆኖ መገኘት
ተልዕኮ
• ለሀገራችን አርሶ አደሮችና ለኢንዱስትሪ ፍጆታ ሸቀጥ አምራቾች የገበያ ዕድል መፍጠር
• የተመረጡ የእህልና ቡና፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት
• የግብርና ምርቶችን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማስፋት
• በሀገራችን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የንግድ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ
• ለልዩ ልዩ ድርጅቶችና ተቋማት የውክልና ግዥና የማማከር አገልግሎት መስጠ
ዕሴቶች
- ተደራሽነት
- የሕግ የበላይነት
- ግልጸኝነት
- ደንበኛ ተኮር መሆን
- ተጠያቂነት
- ብቃትና ውጤታማነት
- የቡድን ሥራ
- የኅብረተሰብ አጋርነት
ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች
- የተመረጡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችንና፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር በተወዳዳሪ ዋጋ ገዝቶ በማሰራጨት የአገር ውስጥ ገበያን ማረጋጋት፤
- ሰብል፣ አትክልት እና ፍራፍሬ በተመረጠ አኳኋን ማስመረት፣ መግዛትና ማሰራጨት፤ ክምችት መያዝ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ ማቅረብ፤
- በወቅታዊ የገበያ መረጃ ላይ ተመስርቶ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ግዢዎችን መፈፀም፣ መሸጥ፤
- የአርሶ አደሩ የማምረት ፍላጎት እንዲያድግ ለግብርና ምርቶች አስተማማኝ ገበያ እንዲፈጠር እገዛ ማድረግ፤
- ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የግብይት አሠራር መዘርጋትና መፈፀም፤
- ለሥራው የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የምርምር፣ የትምህርትና የስልጠና ተቋማት ጋር መተባበር፤
- የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግዢዎችን በሚመለከት የምክር አገልግሎት መስጠት፣ የውክልና ግዢ መፈፀምና ሥልጠና መስጠት፤
- የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ቦንድ የመሸጥ፣ የመግዛት፣ በዋስትና የማስያዝ፤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፤
- ከተቆጣጣሪው ባለስልጣን በሚሰጠው አቅጣጫ ላይ በመመሥረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የሰው ኃብት፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ ሥራ አመራር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለው ኢንቨስትመንት መሳብም ሆነ በኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍን ጨምሮ ጥናት በማካሄድ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን መፈጸም፡፡