ስለ እኛ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክስዮን ማህበር እና የግዥ አገልግሎት ድርጅትን በማቀፍ በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡ |
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለተማሪዎች መማሪያ የሚውል ከሶስት ሚሊየን በላይ መማሪያ ደብተር ከውጭ ሃገር በማስገባት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ ለገበያ የቀረበው ደብተር ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ፣ በቀላሉ ውሃ የማያስገባ...
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከራስ ቴአትር ጋር በመተባበር የ2016 ዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሆስፒታሎች ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማንና ወላጅ እናቶች በዓሉን ምክንያት በማድረግ ስጦታ የማበርከትና የመልካም አዲስ...
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመጪው የ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ለገበያ ካቀረባቸው ምርቶች መካከል የዳቦ ዱቄት (ባለ 10 እና 50 ኪ/ግ)፣...
ከኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣ ዘርፎችና የክልል ግብይት ማዕከላት የተውጣጡ ሠራተኞች “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን አረንጓዴ ዐሻራ የማኖርና በአንድ...
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የደንበኞችና ባለድርሻ አካላት መድረክ ግንቦት 26 እና ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ/ም በሻሸመኔ እና አዳማ ከተሞች ተካሂዷል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የአገልግሎት አሠጣጡን ለማሻሻል በትኩረት ከሚንቀሳቀስባቸው መስኮች አንዱ...
ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓም በቀድሞው ግሎባል በአሁኑ የኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው የምስጋና ዕውቅና መርሃ ግብር ኮርፖሬሽኑ በ2015 ዓ/ም በተካሄደው 8ኛው የካይዘን ዓመታዊ የሽልማት ውድድር በካይዘን ትግበራና ውጤታማነት በአገልግሎት ዘርፍ 3ኛ...