የፕሬስ መግለጫ

ጥቅምት 21 ቀን 2016 /

አዲስ አበባ

ኮርፖሬሽኑ 2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 483,427 ኩንታል ምርት ለገበያ አቀረበ

 

የግዥ አፈጻጸም

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ በአጠቃላይ ሊገዛው ያቀደው መሠረታዊ የምርት አቅርቦት መጠን ብር 1,442,305,115 ዋጋ ያለው 297,648 ኩንታል ሲሆን ብር 2,778,723,940 ዋጋ ያለው 497,993 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 167 በመቶ በዋጋ ደግሞ የዕቅዱን 193 በመቶ አከናውኗል፡፡

የሽያጭ አፈፃፀም

ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ብር 2,920,244,100 ዋጋ ያለው 543,820 ኩንታል መሠረታዊ ምርት ለማሰራጨት አቅዶ ብር 2,665,653,200 ዋጋ ያለው 483,427 ኩንታል ምርትና አገልግሎት በማሰራጨት ዕቅዱን በመጠን 89 በመቶ በዋጋ ደግሞ 91 በመቶ አከናውኗል፡፡

በሀገር ውስጥ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ብር 2,615,940,310 ዋጋ ያለው 468,608 ኩንታል ምርትና የአገልግሎት ሽያጭ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ አቅዶ ብር 2,538,376,639 ዋጋ ያለው 462,237 ኩንታል ምርት ስርጭት በማከናወን የዕቅዱን በመጠን 99 በመቶ በዋጋ ደግሞ 97 በመቶ አከናውኗል፡፡

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ በውጭ ገበያ /ኤክስፖርት/ 75,212 ኩንታል እህልና ቡና በብር 304,303,790 ለመሸጥ አቅዶ 21,190 ኩንታል የተለያዩ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች እና ቡና በብር 127,276,561 (1,029,989 የአሜሪካን ዶላር) በመሸጥ የተጀመረውን ግብይት ማስቀጠል ተችሏል፡፡

ገበያን ለማረጋጋት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ኮርፖሬሽኑ አምራቹ ላመረተው ምርት ገበያ እንዲያገኝ በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ለቀጣይ እንዲበረታታ ለማድረግ ምርቱን በመረከብ፣ እንዲሁም ሸማቹ ህብረተሰብ በአቅርቦት እጥረትና በገበያ ዋጋ መናር እንዳይጎዳ በቂ ምርት ካለበት እጥረት ወዳለበት በማጓጓዝና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ሰፊ የሆነ ሚና ይጫወታል፡፡

ለአምራቹ ምርት ገበያ በመፍጠር የተከናወኑ ተግባራት፡-

ለአርሶ አደሩ ምርት የገበያ ዕድል መፍጠር፡- ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመቱ በአብዛኛው ወቅቱ የክረምት ወራት የነበረ በመሆኑ ምርት ወደ ገበያ በብዛት የማይቀርብ ቢሆንም 368,318 ኩንታል እህልና 755 ኩንታል ቡና እንዲሁም 15,841 ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ ከምርት አቅራቢዎች ግዥ ፈጽሟል፡፡

ለፋብሪካ ምርቶች የገበያ ዕድል መፍጠር፡- የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ያመረቱትን ምርት በመረከብ በሩብ ዓመቱ ውስጥ ብር 315,061,156 ዋጋ ያለው 71,824 ኩንታል ምርት በመግዛት ኮርፖሬሽኑ የገበያ ዕድል ፈጥሯል፡፡

የአቅርቦት እጥረትንና የዋጋ ንረት ለመከላከል የተደረገ ጥረት፡- ኮርፖሬሽኑ የምርት አቅርቦት እጥረትንና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ገበያውን ለማረጋጋት ያደረገው የምርት ስርጭት ሲታይ ለመንግሥት ሠራተኞች፣ ለማረሚያ ቤቶችና ሌሎች ሸማች የህብረተሰብ ክፍሎች 8,373 ኩንታል ጤፍ፣ 14,063 ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ፣ 5,351,200 ሊትር የምግብ ዘይት፣ 19,789 ኩንታል ስኳር፣ 27,527 ኩንታል ልዩ ልዩ የፍጆታ ሸቀጦች ለህብረተሰቡ በማሰራጨት የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተጎጂ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የምርት አቅርቦት እጥረትን ለመሸፈን በተለይም ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ ለዓለም ምግብ ፕሮግራምና ለግብርና ሚኒስቴር ለሴፍትኔት ፕሮግራም ብር 126,603,130 ዋጋ ያለው 37,705 ኩንታል በቆሎ አሠራጭቷል፡፡ ስንዴ በውጭ ምንዛሪ አቅርቧል፡፡ እንዲሁም በግንባታው ዘርፍ እየገጠመ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የስሚንቶ አቅርቦት እጥረትና ዋጋ መናር ለመከላከል ከፋብሪካዎች 126,125,621 ዋጋ ያለው 19,789 ኩንታል በቀጥታ በመረከብ ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ማስራጨት ተችሏል፡፡

ገበያማረጋጋት አስተዋፅኦ በገንዘብ ሲመዘን

በሩብ ዓመቱ በነበሩ ልዩ ልዩ በዓላት ጭምር ሸማቹ ማህበረሰብ በርካታ የፍጆታና ሌሎች ሸቀጦች ግዥ በስፋት የሚያከናውንበት ሁኔታን ኮርፖሬሽኑ በመገንዘብና አስቀድሞ ዝግጅት በማድረግ ገበያዉን ለማረጋገት የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በዚህ መሠረት ፓልም የምግብ ዘይት 5,351,300 ሊትር፣ ፈሳሽ ዘይት 47,900 ሊትር፣ ስኳር 19,789 ኩንታል፣ ሩዝ 11,974 ኩንታል፣ ቀይ ሽንኩርት 113 ኩንታል፣ ጤፍ 8,373 ኩንታል ምርት በማቅረብ ከገበያው ዋጋ አንጻር በጠቅላላ ብር 926,519,196 ቅናሽ ያለው ሥርጭት በማድረግ ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡