የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ

 

የኢንሥኮ የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ በዋነኝነት የተመረጡ የብርዕ፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን እንዲሁም ቡናን ከአገር ውስጥ አምራቾች በመግዛት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡ በዚህም አርሶ አደሩ የእህል ማምረት ፍላጎቱን በማሳደግና ገበያ መፍጠር፣ ለህብረተሰቡም የእህል ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ግብይቱን ለማድረግ ይሠራል፡፡ ለሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት ለልዩ ልዩ ተቋማት የግብርና ምርቶች አቅርቦት ያካሂዳል፡፡

ለሀገር ውስጥ ገበያ ማረጋጊያ የሚውሉ የምግብ እህሎች

 • ጤፍ
 • የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ስንዴ
 • በቆሎና ገብስ

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች

 • የታጠበ ቡና (የሲዳማ፣ የይርጋጨፌ፣ የነቀምት፣ የሊሙ)
 • ያልታጠበ ቡና (የሐረር፣ የሲዳማ፣ የጅማ፣ የቴፒ፣ የነቀምት)
 • የቅባት እህሎች (ነጭ የወለጋና የሁመራ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ተልባ)
 • ጥራጥሬ (ነጭና ቀይ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ፣ ሽምብራ)

ምርት አቅራቢዎች

 • የአርሶ አደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት
 • የመንግሥትና የግል አምራቾች

የወጪ ንግድ መዳረሻዎች

 • ቻይና፣ ፈረንሣይ፣ ኮሪያ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ ጅቡቲ፣ ቤልጅየም፣ ዱባይ

የግብይት ቦታዎች

 • በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያቤት የውጭ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ሽያጭ የሚከናወን ሲሆን በሁሉም ክልሎች ባሉ 122 ክልሎች ግብይት ማዕከላትና ጣቢያዎች የውጭ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ግብይት ይከናወናል፡፡

የግብይት ማዕከላት

አዲስ አበባ ዙሪያ ግብይት ማዕከል --> 0114 16 17 99

አዳማ ግብይት ማዕከል --> 0221 11 11 77

ሻሸመኔ ግብይት ማዕከል --> 0461 10 42 35

ነቀምት ግብይት ማዕከል --> 0576 61 10 17

ደ/ማስቆስ ግብይት ማዕከል --> 0587 71 10 38

ባህር ዳር ግብይት ማዕከል --> 0582 20 01 15

አሰላ ግብይት ማዕከል --> 0223 31 10 78

ደሴ ግብይት ማዕከል --> 0331 11 17 33

ጅማ ግብይት ማዕከል --> 0471 11 09 73

መቀሌ ግብይት ማዕከል --> 0344 41 33 59

ድሬደዋ ግብይት ማዕከል --> 0251 11 20 45

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ: +251114167884/68

ፋክስ: +251114704373