ስለ እኛ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክስዮን ማህበር እና የግዥ አገልግሎት ድርጅትን በማቀፍ በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡
|
![]() |
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሠራተኞች በአራተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “የገበያ ማረጋጊያ ሥራችንን እያጠናከርን አረንጓዴ አሻራችንን እናሣርፋለን” በሚል መሪ ቃል ሆለታ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግብይት ማዕከል የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡ ከተለያዩ...
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አብረውት ከሚሰሩ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የምክክር መድረክ ሰኔ 15/ 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሄደ፡፡ በመድረኩ ላይ ከኮርፖሬሽኑ ጋር...
በሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ሥልጠና ከኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤትና ከንግድ ሥራ ዘርፎች ለተውጣጡና በተለያዩ መደቦች ላይ ለሚሠሩ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ከግንቦት 9-12/2014 ዓ/ም በሁለት ዙር በዋናው...